Our Managment Teams

Teklehaimanot General Hospital has a centralized governance where dedicated and visionary managers have leadership roles to ensure that divisional and sub-divisional units understand and implement the overarching vision of the organization in their daily tasks, and constantly formulate new ways to increase efficiency and quality on all levels of the organization.

Dr.Molla Birhanu Founder & CEO ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል በተመጣጣኝ ክፍያ፣ ጥራት ያለው ሕክምና፣ ርሕራሄና እንክብካቤ በተሞሉ ባለሙያዎቹ እየሰጠ እነሆ ሁለት አስርት ዓመታትን ተጓዘ፡፡ ሆስፒታላችን በታማኝነት ታካሚን ማዕከል ያደረገ አገልግሎትይሰጣል፡፡ ሕሙማንን ተቀዳሚ ያደረገው መርሃችንና አደረጃጀታችን ከሌሎች ሆስፒታሎች የሚለየን መታወቂያችን ሲሆን ዘወትር ለታካሚዎቻችን የሕክምና ጥላና የእክብካቤ ምርኩዝ ለመሆን ጥረታችን አይቋረጥም፡ ፡ የእድገታችን እስትራቴጂ ዋና ምሰሶዎችም ሕሙማንን ያማከለ ሕክምና በላቀ ብቃትና ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች ላይ የተገነቡ በመሆኑ ለወደፊት ራዕያችን መሳካትና ለምናገለግለው ሕዝብ እርካታ እንደሚሆን እናምናለን፡፡
Beza Hailu Co-CEO በመጀመሪያ ህሙማንን ለመርዳት ያላቸውን ከውስጥ የመነጨ ራዕይ ለማስፈፀም ሁሌም በላቀ ትጋትና ቁርጠኝነት ለሚደክሙት የሆስፒታሉ መስራችና ፕሬዝዳንት ለዶ/ር ሞላ ብርሃኑ ያለኝን አክብሮትና ምስጋና መግለፅ እወዳለሁ፡፡ ተምሣሌትነታቸው ለሁሉም የሆስፒታሉ ሠራተኞች የትጋትና የሞራል ምንጭ ሆኗል፡፡ ከዛሬ ሃያ ዓመታት በፊት በመስራቹ ልብ ውስጥ የተፀነሰው ይህ ራዕይ አሁን ላይ ከ400 በላይ ሠራተኞች የሥራ እድል በመፍጠር ለማሕበረሰቡ ደግሞ ተመራጭ ሆስፒታል ለመሆን በቅቷል፡ ፡ ሆስፒታላችን በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ የህሙማንን የሕክምና ፍላጎት ከልብ በመነጨ ርህራሄና እንክብካቤ ለሟሟላት ሁሌም የሚጥር ተቋም ነው፡፡ በምላሹም በአገልግሎታችን ተማምነው፣ ሆስፒታላችንን መርጠው ከመላው ሃገሪቱ በሚመጡ ታካሚዎች ጥልቅ ኩራትና ከባድ ኃላፊነት ይሰማናል፡፡ የሁል ጊዜ ጥረታችን ታካሚዎቻችን ነጥሮ የወጣ ዘመናዊ ሕክምና እንዲያገኙ፣ እናታዊ እንክብካቤ እንዲሰጣቸው፣ በምላሹም የታካሚዎቻችንን እርካታ ማየት ነው፡፡ እስካሁን ለደረስንበት ስኬት ድንቅ የሆኑ የባለሙያዎቻችን ድካምና ጥረት መሆኑ ሐቅ ነው፡፡ የአንድ ተቋም ዋና ስኬት ሁሌም በአላማ፣ በትጋትና በቅንነት በሚያገለግሉ ሠራተኞች ነው
ዶ/ር መክሊት አያሌው Medical Director አብዛኛው ሰው ወደ ሆስፒታል የሚሄደው ለገጠመው የጤና እክል መፍትሄ የሚሰጠው የጤና ባለሙያ ለማግኘት ነው። በህመም ላይ ያሉ ሰዎች አስፈላጊውን ህክምና ከማግኘት በተጨማሪ ከምንጊዜውም በላይ እንክብካቤና ርህራሄ ይሻሉ፡፡ ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታልም ይህን የታክሚዎች ፍላጎት በማሟላት ርገድ ተግቶ ሲሰራ የቆየ አንጋፋ ሆስፒታል ነው። የሁልጊዜ ትኩረታችን በላቀ ጥራትና በልዮ እንክብካቤ የታጀበ አገልግሎት በመስጠት የታካሚዎቻችንን የአገልግሎት እርካታ ማላቅ ነው። ይህንንም ለመተግበር በየደረጃው ያሉ የሆስፒታላችን ባለሙያዎች ሁልጊዜም በትጋት ላይ ናቸው። በሆስፒታላችን ጥራት የማንደራደርበት ቀዳሚ ሃላፊነታችን ሲሆን በየእለቱ ከ 70 በላይ ጠቅላላ፣ ስፔሻሊቲ፣ሰብስፔሻሊቲና ድጋፍ ሰጪ አገልግሎቶችን በጥራትና በቅልጥፍና ይሰጣሉ። እጅግ ዘመናዊ የሆኑት የህክምና መሳሪያዎቻችንም አስተማማኝ ምርመራና ውጤት በመስጠት ለላቀው የህክምና ጥራታችን የድርሻቸውን ይወጣሉ። በተጨማሪም የ ISO 15189:12 የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያገኘው አድቫንስድ ላቦራቶሪያችን፣ በዘመናዊ የህክምና ቴክኖሎጂዎች የተደራጁት የጨቅላ ህጻናትና የአዋቂ ጽኑ ህሙማን ክፍሎቻችን እንዲሁም ምቹና ማራኪ የሆነ ገጽታ ያለው የኩላሊት እጥበት ክፍላችን በማንኛውም ሁኔታ ላይ ያሉ ታካሚውችን ለምርዳት የሚያስችል ብቃት ሰጥተውናል። በአጠቃላይ ሁሌም በትጋት የምንሰራው ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እናታዊ በሆነ መስተንግዶ ና እንክብካቤ በመስጠት የሃገራችንን የህክምና አገልግሎት ደረጃ አንድ እርምጃ ለማራመድ ነው።