ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል

በ1993ዓ.ም ታህሳስ ወር ከፍተኛ ክሊኒክ ሆኖ የጀመረው የጤና ተቋማችን በሚሰጠው ጥራት ያለው አገልግሎት እና በተመጣጣኝ የአገልግሎት ክፍያው በብዙ ደንበኞች ዘንድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን በማትረፉ፣ በ1995ዓ.ም ሚያዚያ ወር ሁለተኛውን ቅርንጫፍ ከፍተኛ ክሊኒክ መክፈቱ ይታወቃል፡፡ በዚህም ሳይገታ አገልግሎቱን በማስፋትና ተጨማሪ ጠቅላላ የሕክምና ዘርፎችን ለተገልጋዮች በማቅረቡ የአገልግሎት ፈላጊዎች እጅግ እየጨመሩ በመምጣታቸው፣ የተገልጋዮችን ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል ባለ 7 ወለል የሆስፒታል ህንፃ በመገንባት በ2004ዓ.ም የካቲት ወር ተህለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል ሆኖ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተደራጅቶ፣ የተሟላ የሕክምና አገልግሎት ከብቁ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ማህበረሰቡን እያገለገለ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል ካፒታል ብር 360,230,750 (ሶስት መቶ ስልሳ ሚሊየን ሁለት መቶ ሰላሳ ሺህ ሰባት ሞቶ ሃምሳ ብር) የደረሰ ሲሆን 332 (ሦስት መቶ ሰላሳ ሁለት) ቋሚ ሠራተኞችን 87 (ሰማንያ ሰባት) የትርፍ ሰዓት ሠራተኞችን እንዲሁም 3 (ሦስት) የኮንትራት ሠራተኞች በስሩ እያስተዳደረ ይገኛል፡፡ ተመጣጣኝ ዋጋችን፣ ለጥራት ያለን ሥፍራ እንዲሁም የታካሚውን ፍላጎት ለሟሟላት የምናደርገው ጥረት እና ለሥነምግባር የምንሰጠዉ ቦታ ለተገልጋዮቻችን የጤና መሻሻልና ፈውስ ተስፋ ነው፡፡ ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል የኑሮ ደረጃ ሳይገድበው ታካሚዎችን ለመርዳት ሁሌም አንድ እርምጃ ይቀድማል፡፡


ራዕይ 

በምስራቅ አፍሪካ ካሉ ተመራጭ የሕክምና ማዕከላት  አንዱ መሆን

ተልዕኮ

ጥራት ያለው አገልግሎት በተመጣጣኝ ክፍያ መስጠት

እሴት

እንክብካቤ አክብሮት ታማኝነትና ርህራሄ ሁሌም ለሁሉም 

 



0
0

"አማርኛ Health is the most important thing you have in life!"

አማርኛ Contact us now to schedule an appointment.

አድራሻ

ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል
ሶማሌተራ, ከ ግሎባል ኢንሹራንስ ፊት ለፊት
አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

የስራ ሰአት

እሁድ - እሁድ 24 ሰአት ክፍት ነን

ለድንገተኛ አደጋ

(+251) 8175

ማህበራዊ ገጾች