ላቦራቶሪ
ከኢትዮጵያ ብሄራዊ አክሬዲቴሽን ጽ/ቤት የISO 15189: 2012 የጥራት ማረጋገጫ ያለዉ አድቫንስድ ላብራቶሪያችን በዘመናዊ ማሽኖች ተደራጅቶ በሳምንት 7 ቀናት ለ24 ሰአታት በሐገር ዉስጥ የማይሰሩ ’የወላጅነት’ (PATERNITY) ምርመራን ጨምሮ SRL ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር ወደ ዉጪ ሐገር አስልኮ ምርመራዎችን ያደርጋል፡፡ላቦራቶሪያችን ስድስት ንዑሳን ክፍሎች አሉት፡፡
ከኢትዮጵያ ብሄራዊ አክሬዲቴሽን ጽ/ቤት የISO 15189: 2012 የጥራት ማረጋገጫ ያለዉ አድቫንስድ ላብራቶሪያችን በዘመናዊ ማሽኖች ተደራጅቶ በሳምንት 7 ቀናት ለ24 ሰአታት በሐገር ዉስጥ የማይሰሩ ’የወላጅነት’ (PATERNITY)
ምርመራን ጨምሮ SRL ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር ወደ ዉጪ ሐገር አስልኮ ምርመራዎችን ያደርጋል፡፡ላቦራቶሪያችን ስድስት ንዑሳን ክፍሎች አሉት፡፡
ሔማቶሎጂ ፡-በዚህ ክፍል በሰአት 225 የተማላ የደም ህዋሳት ምርመራዎችን ማከናወን በሚችሉ
አራት ዘመናዊ
የሄማቶሎጂ አናላይዘሮች HMX Beckman coulter, Sysmex xp-300, Spincell
3, Humacount
30TS በመታገዝ በቀን ከ400
በላይ ናሙናዎችን ያስተናግዳል፡፡
ኢሙኖሎጂ ፡- በዚህ ክፍል በሁለት ኤሌክትሮኬሙሊሚነሰንስ እና ኬሙሊሚነሰንስ ቴክኖሎጂ በሚጠቀሙ ዘመናዊ ኢሚኖ አሴ ማሽኖች Cobas e411 Roche እና Maglumin 800 በመታገዝ በሰዓት ከ368 በላይ ምርመራዎችን የማከናወን አቅም አለው።
ከነዚህም ምርመራዎች በጥቂቱ፡-
- የካንሰር ጠቋሚ
- የማህንነት
- ታይሮይድ ሆርሞንስ
- የደም ቫይረሶች
- የልብ ኢንዛይሞች
ክሊኒካል ኬሚስትሪ ፡- በዚህ ክፍል የተራቀቀ ቴክኖሎጅን በሚጠቀሙ 4 ክሊኒካል ኬሚስትሪ አናላይዘሮች AU 480 Beckman coulter, Cobas-C311 Roche Hitachi, ABX pentra 400,
እና Mindray-BS200 በመታገዝ በሰዓት 1400
ምርመራዎች የማከናወን አቅም አለዉ፡፡
ሞለኪዉላር ፡- በዚህ ክፍል ከግል ሆስፒታሎች የመጀመሪያ የሆነዉንመድሃኒት የተላመደ የቲቢ አምጪ ባክቴሪያ
ምርመራ አምፕሊፊኬሽን እና ዲቴክሽን በመጠቀም በጄንኤክስፐርት ማሽን ይከናወናል፡፡
ቤዚክ ማይክሮስኮፒ ፦ በዚህ ክፍል የደምና የሽንት ምርመራን ጨምሮ የተለያዩ
በሽታ አምጪ ባክቴሪያዎችን
ለመለየት የሚያስችሉ ምርመራዎች
ይከናወናሉ።
ፓቶሎጂ ፡- በዚህ ክፍል የተለያዩ ናሙናዎችን በመዉሰድ ከቀላል ተላላፊ ህመሞች እስከ ከፍተኛ ህመሞች
ለማወቅ እና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ምርመራዎች ይካሄዳሉ፡፡
ከነዚህም ምርመራዎች በጥቂቱ፡- የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ (ፓፕ ስሚር)
የደም ህዋሳት ይዘት ምርመራ /ሞርፎሎጂ/
የሰዉነት ህዋሳት ምርመራ
ባዮፕሲ